A- A A+

አርስተ ዜና
  • Loading

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ (የመጀመሪያ ረቂቅ)

User Rating: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

መግቢያ

መገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ፣ በማሳወቅ፣ በማስተማርና በማዝናናት እንዲሁም የዜጎችን ሀሳብን የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ በማድረግ እና የተለያዩ አመለካከቶችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ ለዲሞክራሲ ስርዓት መዳበር እና ተፈላጊ የሆነውን ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ ነፃነት የተረጋገጠና ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶችን የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚመራበት ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ባለመኖሩ ዘርፉን በብቃት እና በጥራት በማስፋፋት ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎች የመረጃ ተደራሽ ለማድረግ አልተቻለም፡፡

ሙሉውን የሚከተለውን ሊንክ ጠቅ በማድረግ በ PDF ይመልከቱ። የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ (የመጀመሪያ ረቂቅ)

 

 

ስለ ብሮድካሥት ባለሥልጣን አንዳንድ ነገር

User Rating: 2 / 5

Star ActiveStar ActiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በሀገራችን ለበርካታ ዘመናት መገናኛ ብዙኃን ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታነት ውጭ እምብዛም ለህዝብና ሀገር ጥቅም ሲውሉ አይታይም ነበር፡፡ በዚህ ሶስት 10 ዓመታት የተፈጠረው አዲስ የሚዲያ ነፃነት ተከትሎ በዓይነትና በባለቤትነት ሁኔታ እየተበራከተ መጥቷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሚዲያው ኢንዱስትሪ ከአንድ ወገን ሃሳብና እምነት ማሰራጨት ወጥቶ የብዙሃን አስተሳሰብና እምነት ማንሸራሸሪያነት መድረክ ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡

ከስር የተገለፀው መረጃም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የሚዲያ ብዙሃነትና ተደራሽነት ለማስፋፋት ባደረገው ጥረት መሰረት በሃገራችን ፈቃድ የተሰጣቸው የብሮድካስት አገልግሎት ሚዲያዎች ዓይነትና ብዛት ምን እንደሚመስል የሚሳይ ነው፡፡

  የብሮድካሥት ሚዲያ ዕድገት ንፅፅር ከባለቤትነት አንፃር
ተቁ የባለቤትነት ሁኔታ ከ1983 ዓ.ም በፊት ከ1983 በኋላ   ምርመራ
ሬዲዮ ቴሌቭዥን ሬዲዮ ቴሌቭዥን  
ቴሪስተሪያል ሳተላይት ሳተላይት ቴሪስተሪያል
1 የህዝብ 1 1 10 5 8 3  
2 የንግድ ­­--- ­--- 12 (23 ቅርንጫፍ ጣቢያዎች) ­­--- 18 ---

     9 ሬዲዮና 14 ተሌቭዝን ጣቢያዎች በመደበኛ ስርጭት ላይ፤

      3 ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሙከራ ስርጭት ላይ፤

      3 ሬዲዮና 1 ቴሌቪዥን በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

3 የማኅበረሰብ ­­--- ­--- 49 ­­--- ­--- --- 31 ጣቢያዎች በስርጭት ላይ እና 18 በሂደት ይገኛል ላይ
ድምር 1 1 71 5 26 3  
                   
JoomShaper