A- A A+

ባለስልጣኑ ከህዝብ ክንፍ ጋር በመተባበር የህዝብን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላትና በሚዲያዎች የሚታየውን የሚዛናዊነት ችግር አዝማሚያ መስመር ለማስያዝ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

User Rating: 1 / 5

Star ActiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 

ህዳር 05 ቀን 2011 ዓ/ም  

ኢ.ብ.ባ

የባለስልጣኑ የማኔጅመንት አባላት ህዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ምንነትና የመጀመርያው መንፈቀ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሂደት በሚመለከት ከህዝብ ክንፍ ጋር የሚያተዋወቅ የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡  

በዚሁ መድረክ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርበማድረግ ውይይቱን የመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ህብረተሰብ ሚዛኑን የጠበቀ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤታማ የሚሆነው የተቀናጀ የህዝብና መንግስት ጥረት ሲከናወን መሆኑን በመጥቀስ ይህ እውን ሊሆን የሚችለው ባለስልጣኑ በሚያደርጋቸው የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ዘወትር ከጎኑ የማይለዩትን የህዝብ ክንፍ አባላት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ጠንካራ ድጋፋቸውን ሲያበረክቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ክንፍ አባላት በባለስልጣኑ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድና በመጀመርያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሂደት ላይ እንዲወያዩ ማድረግ ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ህብረተሰቡ በሚዲያ ሬጉላቶሪ ሥራ ላይ ተሳታፊ በማድረግ ሚዛናዊና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና ባለስልጣኑ ለህብረተሰቡ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ምንነት በማስረዳት ለውጤታማነታቸው በጋራ መንቀሳቀስ ለማስቻል ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ በተለይ በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚመለከቱ መረጃዎች ሚዛናዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ የህብረተሰቡን የጋራ እምነትና አመለካከት በማይሸረሽር መልኩ እንዲቀርቡ በማድረግ በኩል የህዝብ ክንፍ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

አይይዘውም በተለያዩ ሚዲያዎች የሚተላለፉት የፕሮግራም እና የማስታወቂያ ይዘቶች ወቅታዊነት ሚዛናዊነትና ተአማኒነት በመመዘን ዝንፈት ሲያጋጥም ወቅታዊና ተገቢ እርምት እንዲወሰድባቸው በማድረግ በኩል የህዝብ ክንፍ ሚናና ተሳትፎ ወሳኝ ነው በማለት አስረድዋል፡፡ በመሆኑም ለህዝባችን ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ተደራሽነት፣ ለሃገራችንና ለህዝባችን ሰላም መከበርና በአካልና በጠንካራ ስነልቦናዊ ማንናት የጠነከረና የሥነ ምግባር ጉድለትን የሚፀየፍ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁላችንም በተቀናጀ መልኩ የድርሻችን ልንወጣ ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

ይህ መድረክ የመተዋወቂያም በመካከላችን ያለው ተከታታይንት የግንኝነት መስመር የምናጠናክርበት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተር ወደፊት በተቋሙ አሠራርና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታዩ ባሉት የሚዲያዎች የዘገባ አዝማሚያዎች በሚመለከት በማንኛውም ቦታና ጊዜ የምትሰጧቸው አስተያየትና ጥቆማዎች ባለስልጣኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት መሻሻል የሚያግዙና በክብር የምንቀበላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የሚዲያው ኢንዲስትሪ ባደገባቸው ሃገራት የሚዲያዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች በመከታተልና በመቆጣጠር ረገድ ያለው ተሞክሮ ሲታይ በቁጥጥርና ቅጣት ብቻ ዘርፉ ማሻሻል እንደማይቻል እና ይልቁንም በዚህ ዙርያ የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ ያሳያል፡፡

በመሆኑም በሃገራችንም ያለህዝብ ተሳትፎ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ውጤታማ ፍሬ ማግኘት ስለማይቻል ለዘርፉ ዕድገትና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ሁላችንም በጋራ ልንረባረብ ይገባል ሲሉ በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡

ከልዩ ልዩ ተቋማት ተውጣጥተው በውይይቱ ላይ የተገኙት የህዝብ ክንፍ አባላት በበኩላቸው ከነሱ የሚጠበቀውን ጠንካራ ተሳትፎ ማበርከት እንዲችሉ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ብለው የሚያምኑባቸውን ሃሳቦች ያቀረቡ ሲሆን ተሳትፎአቸው በሚፈለገው መንገድ ተጠናክሮ ከነሱ የሚጠበቀውን ሚና መወጣት እንዲችሉ ዓቅማቸውን መገንባት የሚችሉባቸው ልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ቢዘጋጁላቸው መልካም መሆኑን አስምረውበታል፡፡

በመጨረሻም የዘርፉን መሻሻል አልመው በተሰብሳቢዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች አመስግነው የተገኙትን ልምድና ተሞክሮዎች በመቀመር ወደፊት በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ መስርያ ቤቱ ለሁሉም የህዝብ ክንፍ አባላት ሁሌም ክፍት መሆኑን በመግለፅ ሃሳብና አስተያየታቸውን እንዲሁም ጥቆማዎቻቸውን በማንኛውም ሰዓት ሊያካፍሉ እንደሚችሉ አሳስበው ወደፊት የአባላቱን አቅም የሚገነባባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደሚኖሩም ቃል ገብተዋል፡፡

                                         የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Add comment


Security code
Refresh

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን  ለፖለቲካ ፓርቲዎች የደለደለውን የአየር ሰዓትና የጋዜጣ  አምድ እጣ ይፋ አደረገ።

09.04.2021

የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ፣የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ኃላፊዎች፣የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች በተገኙበት ተከናውኗል። በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሚወዳደሩ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ57 የመገናኛ ብዙሃን ላይ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ዕጣ ወጥቷል፡፡ ቀደም ሲል ከነበረው የምርጫ ዘመን በቴሌቪዥን 300%   በሬዲዮ 40% ጭማሪ የአየር ሰዓት መመደቡ ታውቋል ። ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምረጡኝ ቅስቀሳ የተመደበው ነጻ የአ
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት  ሐላፊዎችን የእንጦጦ ፓርክን አስጎበኘ

21.10.2020

ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም አዲስ አበባ. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትላንት ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ የአለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የተለያዩ የመንግስት ሐላፊዎችን ያካተተ ጉብኝት በእንጦጦ ፓርክ አካሒዷል። የጉብኝቱ አላማ ድንበር ዘለል ጋዜጠኞችንና የመንግስት የመረጃ ምንጭ የሆኑ ሐላፊዎችን በማቀራረብ መንግስት መረጃን ለመስጠት በሩ ክፍት እንደሆነና ጋዜጠኞቹ በመረጃ እጥረት ምክንያት ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እንዳያደርሱ ማድረግ መሆኑን የባለስልጣ
በሥነ-ምግባር ህጎችና መርሆዎች ዙሪያ ለበለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

16.10.2020

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ምንነት፤ህጎችና መርሆዎች ላይ ያተኮረ በሶስት ዙር የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጠ :: በሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ  ተድላ ከጥቅምት 4-6 /2013 ዓ.ም በመ/ቤቱ አዳራሽ  የተሰጠው ስልጠና ዋንኛ ትኩረቱ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ህጎችና መርሆዎች በመታገዝ የተሰጣቸውን የስራ ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መሆኑን በስልጠናው ወቅት ገልጸዋል ፡፡    አ
ባለስልጣኑ በሃገራችን ሚዲያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

30.09.2019

ባለስልጣኑ በሃገራችን ሚዲያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት(UNDP)ጋር በመተባበር ˝የሃገራችን ሚዲያ በህዝብ እይታ ምን ይመስላል ˝ በሚል መሪ ሃሳብ ከመስከረም 14-15/01/12 ዓ.ም ከደቡብ ክልል ከተሞችና ከኦሮሚያ ክልል ምዕ/አርሲ ዞን ከተወጣጡ፤ከዞንና ወረዳ አመራሮች፤ ከሃገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በሻሸመኔ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ
ባለሥልጣኑ  ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች የቴክኒክ ስልጠና ሰጠ

04.07.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን  ከተለያዩ የማህበረሰብ ሬዲዮ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች  ከሰኔ 24-25/2011 ዓ.ም. የቴክኒክ ስልጠና  ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ሰጥቷል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የጥናትና ስልጠና ማዕከል ስራ አስፈጻሚ  አቶ ዳንኤል በቀለ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት አሁን ያለውን አገራዊ ለውጥ ለማስፋት እንዲቻል የማህበረሰብ ሬዲዮዎች አቅም መጎልበት ይኖርበታል፡፡ ይህ የለውጥ  መረጃ  ለሁሉም ህብረተሰብ ሊዳረስ የሚችለ
ማስታወቂያ ከሚሰጠው ጠቀሜታና ከሚያሳድረው ጉዳት አንፃር ተመዝኖ ሊቀርብ ይገባል ተባለ

27.05.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከምግብ፣ መድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአልኮል ማስታወቂያ ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃንና ከማስታወቂያ ወኪሎች ጋር ከግንቦት 15-16/2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ የውይይቱ ዋነኛ አላማም የአዋጁን ድንጋጌዎች ለማስታወቂያ አዘጋጆች፣ አሰራጮች፣ አስነጋሪዎች እና ለሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ባለድርሻ አካላት በማቅረብና ግንዛቤ በመፍጠር ለአዋጁ ተግባራዊነት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የባለ
ባለስልጣኑ ሚዲያን በተቆጣጣሪነት መንፈስ ለማስተካከል ጥረት ከማድረግ ይልቅ የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ተባለ፡፡

07.05.2019

ባለስልጣኑ ሚዲያን በተቆጣጣሪነት መንፈስ ለማስተካከል ጥረት ከማድረግ ይልቅ የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የፕረስ ነፃነት ቀንን በፓናል ውይይት አክብሮ ውሏል፡፡ በዓሉ “ሚዲያ ለዲሞክራሲ፡- ጋዜጠኝነትና ምርጫ በዘመነ መረጃ ብክለት” (“Media for Democracy; Journalism and Elections in Times of Disinformation”) በሚል ዓ
ባለስልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን አቅም የማጎልበት ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ተባለ

08.04.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጋር በመተባበር የፍ/ቤትና የፍርድ ሂደት ነክ ጉዳዮችን አዘጋግብ በተመለከተ ከመጋቢት 26-27/7/11 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት መገናኛ ብዙሃን እርስ በርሳቸው በመተራረም ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ተቋሙ ድጋፍና ክትትል ከማ
መገናኛ ብዙሃን ኃላፊነት በሚሰማዉ አካል ካልተያዙና በህግ ካልተመሩ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው  ያመዝናል ተባለ፤

21.03.2019

  የመገናኛ ብዙሃን የህግ ማዕቀፍና የሚዲያ ባለሙያዎች ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲሁም ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ከተቋሙ ባለሙያዎች ምን ይጠበቃል? በሚሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከመጋቢት 2-10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡   የህግና ማስታወቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ስልጠናውን ሲሰጡ እንደተናገሩት መገናኛ ብዙሃን ለህዝቡ መረጃ በመስጠት፤ በማስተማርና በማዝናናት ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታ
የተቋሙን ተልዕኮ እውን ለማድረግ የህዝብ ክንፉ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ተባለ

15.03.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የህዝብ ክንፉን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊያጎለብቱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከመጋቢት 3-5/07/2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር በመወከል ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገ/ጊዮርጊስ አብርሃ እንዳሉት ተቋሙ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶችን ሲያከናውን የህዝብ ክንፉን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡ የባለስልጣኑ ተልዕኮ «የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በመ
JoomShaper