A- A A+

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት ሐላፊዎችን የእንጦጦ ፓርክን አስጎበኘ

User Rating: 0 / 5

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 

ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም አዲስ አበባ. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትላንት ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ የአለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የተለያዩ የመንግስት ሐላፊዎችን ያካተተ ጉብኝት በእንጦጦ ፓርክ አካሒዷል።

የጉብኝቱ አላማ ድንበር ዘለል ጋዜጠኞችንና የመንግስት የመረጃ ምንጭ የሆኑ ሐላፊዎችን በማቀራረብ መንግስት መረጃን ለመስጠት በሩ ክፍት እንደሆነና ጋዜጠኞቹ በመረጃ እጥረት ምክንያት ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እንዳያደርሱ ማድረግ መሆኑን የባለስልጣኑ መ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ ተናግረዋል።

በጉብኝቱከተሳተፉት..አልጀዚራ እና ኒዮርክ ታይምስን ጨምሮ በአሜሪካ፣በብሪታኒያ፣በቻይና፣በፈረንሳይ፣ቱርክና በማዕክላዊ ምስራቅ አገራት ለሚገኙ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚዘግቡ የሃገር ውስጥ ወኪል ጋዜጠኞች ይገኙበታል

ከሐገር ውስጥም የመ/ቤቱን ዋና ዳይሬክተር ጨምሮ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ሐላፊ ቢኪላ ሁሪሳ አና ሌሎች የመንግስት ሐላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ተፈጥሯዊ መልክአ ምድርን መሰረት አድርጎ የፈጠራ ችሎታና ጥበብ የታከለባቸው ስራዎችን አድንቀዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለስልጣን መ/ቤቱ የአለም አቀፉ ጋዜጠኞችን በጉብኝት መልክ ከመንግስት ሐላፊዎች ጋር ለማቀራረብ የሰራው ስራ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን ገልፀው ወደፊት ተመሳሳይ ጉብኝቶችን ከመዲናው ውጪ ቢደረጉ የኢትዮጵያን ክንውኖች በሚዛናዊ እይታ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ማድረስ ያስችላል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ሐላፊ የሆኑት ዶ/ር ቢኪላ ሁሪሳ መንግስት ከምን ግዜም በላይ ለመረጃ ክፍት መሆኑን ጋዜጠኞቹ በማንኛውም ሰዓት መረጃ ሲፈልጉ ወደ ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ ጋር ለማገናኘት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በፓርኩ ኪሚገኙ ባህላዊ የኩሪፍቱ ሬስቶራንት የምግብና መጠጥ ግብዣ በተካሄደበት ወቅት ጋዜጠኞችና የመንግስት ሃላፊዎች አንድ ለአንድ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ----ጋዜጠኞቹ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባደረገው ጥረት እንደተደሰቱና መንግስት ለመረጃ ክፍት ለመሆን ያለው ዝግጁነት በጎ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።

Add comment


Security code
Refresh

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን  ለፖለቲካ ፓርቲዎች የደለደለውን የአየር ሰዓትና የጋዜጣ  አምድ እጣ ይፋ አደረገ።

09.04.2021

የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ፣የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ኃላፊዎች፣የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች በተገኙበት ተከናውኗል። በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሚወዳደሩ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ57 የመገናኛ ብዙሃን ላይ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ዕጣ ወጥቷል፡፡ ቀደም ሲል ከነበረው የምርጫ ዘመን በቴሌቪዥን 300%   በሬዲዮ 40% ጭማሪ የአየር ሰዓት መመደቡ ታውቋል ። ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምረጡኝ ቅስቀሳ የተመደበው ነጻ የአ
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የመንግስት  ሐላፊዎችን የእንጦጦ ፓርክን አስጎበኘ

21.10.2020

ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም አዲስ አበባ. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትላንት ማክሰኞ 9-2013 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ የአለም አቀፍ ጋዜጠኞችንና የተለያዩ የመንግስት ሐላፊዎችን ያካተተ ጉብኝት በእንጦጦ ፓርክ አካሒዷል። የጉብኝቱ አላማ ድንበር ዘለል ጋዜጠኞችንና የመንግስት የመረጃ ምንጭ የሆኑ ሐላፊዎችን በማቀራረብ መንግስት መረጃን ለመስጠት በሩ ክፍት እንደሆነና ጋዜጠኞቹ በመረጃ እጥረት ምክንያት ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እንዳያደርሱ ማድረግ መሆኑን የባለስልጣ
በሥነ-ምግባር ህጎችና መርሆዎች ዙሪያ ለበለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

16.10.2020

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ምንነት፤ህጎችና መርሆዎች ላይ ያተኮረ በሶስት ዙር የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጠ :: በሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ  ተድላ ከጥቅምት 4-6 /2013 ዓ.ም በመ/ቤቱ አዳራሽ  የተሰጠው ስልጠና ዋንኛ ትኩረቱ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሥነ-ምግባር ህጎችና መርሆዎች በመታገዝ የተሰጣቸውን የስራ ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መሆኑን በስልጠናው ወቅት ገልጸዋል ፡፡    አ
ባለስልጣኑ በሃገራችን ሚዲያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

30.09.2019

ባለስልጣኑ በሃገራችን ሚዲያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት(UNDP)ጋር በመተባበር ˝የሃገራችን ሚዲያ በህዝብ እይታ ምን ይመስላል ˝ በሚል መሪ ሃሳብ ከመስከረም 14-15/01/12 ዓ.ም ከደቡብ ክልል ከተሞችና ከኦሮሚያ ክልል ምዕ/አርሲ ዞን ከተወጣጡ፤ከዞንና ወረዳ አመራሮች፤ ከሃገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በሻሸመኔ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ
ባለሥልጣኑ  ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች የቴክኒክ ስልጠና ሰጠ

04.07.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን  ከተለያዩ የማህበረሰብ ሬዲዮ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች  ከሰኔ 24-25/2011 ዓ.ም. የቴክኒክ ስልጠና  ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ሰጥቷል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የጥናትና ስልጠና ማዕከል ስራ አስፈጻሚ  አቶ ዳንኤል በቀለ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት አሁን ያለውን አገራዊ ለውጥ ለማስፋት እንዲቻል የማህበረሰብ ሬዲዮዎች አቅም መጎልበት ይኖርበታል፡፡ ይህ የለውጥ  መረጃ  ለሁሉም ህብረተሰብ ሊዳረስ የሚችለ
ማስታወቂያ ከሚሰጠው ጠቀሜታና ከሚያሳድረው ጉዳት አንፃር ተመዝኖ ሊቀርብ ይገባል ተባለ

27.05.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከምግብ፣ መድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአልኮል ማስታወቂያ ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃንና ከማስታወቂያ ወኪሎች ጋር ከግንቦት 15-16/2011 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ የውይይቱ ዋነኛ አላማም የአዋጁን ድንጋጌዎች ለማስታወቂያ አዘጋጆች፣ አሰራጮች፣ አስነጋሪዎች እና ለሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ባለድርሻ አካላት በማቅረብና ግንዛቤ በመፍጠር ለአዋጁ ተግባራዊነት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የባለ
ባለስልጣኑ ሚዲያን በተቆጣጣሪነት መንፈስ ለማስተካከል ጥረት ከማድረግ ይልቅ የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ተባለ፡፡

07.05.2019

ባለስልጣኑ ሚዲያን በተቆጣጣሪነት መንፈስ ለማስተካከል ጥረት ከማድረግ ይልቅ የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የፕረስ ነፃነት ቀንን በፓናል ውይይት አክብሮ ውሏል፡፡ በዓሉ “ሚዲያ ለዲሞክራሲ፡- ጋዜጠኝነትና ምርጫ በዘመነ መረጃ ብክለት” (“Media for Democracy; Journalism and Elections in Times of Disinformation”) በሚል ዓ
ባለስልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን አቅም የማጎልበት ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ተባለ

08.04.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጋር በመተባበር የፍ/ቤትና የፍርድ ሂደት ነክ ጉዳዮችን አዘጋግብ በተመለከተ ከመጋቢት 26-27/7/11 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት መገናኛ ብዙሃን እርስ በርሳቸው በመተራረም ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ተቋሙ ድጋፍና ክትትል ከማ
መገናኛ ብዙሃን ኃላፊነት በሚሰማዉ አካል ካልተያዙና በህግ ካልተመሩ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው  ያመዝናል ተባለ፤

21.03.2019

  የመገናኛ ብዙሃን የህግ ማዕቀፍና የሚዲያ ባለሙያዎች ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲሁም ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ እውን ለማድረግ ከተቋሙ ባለሙያዎች ምን ይጠበቃል? በሚሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከመጋቢት 2-10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡   የህግና ማስታወቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ስልጠናውን ሲሰጡ እንደተናገሩት መገናኛ ብዙሃን ለህዝቡ መረጃ በመስጠት፤ በማስተማርና በማዝናናት ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታ
የተቋሙን ተልዕኮ እውን ለማድረግ የህዝብ ክንፉ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ተባለ

15.03.2019

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የህዝብ ክንፉን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊያጎለብቱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከመጋቢት 3-5/07/2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር በመወከል ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገ/ጊዮርጊስ አብርሃ እንዳሉት ተቋሙ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶችን ሲያከናውን የህዝብ ክንፉን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡ የባለስልጣኑ ተልዕኮ «የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በመ
JoomShaper