ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኢ.መ.ብ.ባ)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩ ዓላማ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸው ይዘቶች በሀገራችን ተከብሮ የቆየውን የሃይማኖት መቻቻልና አብሮነት ለማጠናከር እንዲሁም በሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ እንዳሉት የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ግብረ ገብነትን በማስተማር ትውልድን ከማነፅ በተጨማሪ የጋራ እሴቶች እንዲጠናከሩ፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ስለሆነም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን በአስተምሮታቸው አሁን ላለንበት ችግር መፍትሄ በሚያመጣ ፣ ሀገር በሚገነባና መልካም ዜጋን በሚያንፅ ጉዳይ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የአብሮነት አሴቶችን በማጠናከር እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ሊጫወቱት ስለሚገባው ሚና እንዲሁም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የህግ ማዕቀፎች የሚሉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለምዝገባ የሚየስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ምዝገባ ላከናወኑ ለ23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ሰርተፊኬት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ውይይቱ ተጠናቋል።
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ
ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት
የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ "ክህሎት ለሁለንተናዊ ስኬት" በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ተጠቆመ፡፡
ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡