Asset Publisher

null አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ-ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ

ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ የቆዩ አስር አንጋፋ ባለሙያዎች እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የእድገት የሃሳብ ፎኖተ-ካርታ ላይ ምክክር እደርገዋል፡፡

የሚዲያው እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ ያተኮረው ውይይት መድረክ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተዘጋጀ ሲሆን አራተኛውየመንገስት አካል እስከመባልየደረሰው ተፅኖ ፈጣሪ ዘርፍ የሚመራበትን አቅጣጫ በአንጋፋዎቹ እይታ ውስጥ ለመመልከት ነው፡፡

አንጋፋ ሙሁራኑ መገናኛ ብዙኃን በአሁን ሰዓት በብዙ እድሎች የታጀበ ሆኖ ሳለ የህብረተሰቡን ስነ ልቦና እና በሃገሪቱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በተቀናጀ መልኩ መስራት ላይ ትልቅ ክፍተት እንደሚታይ ያነሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባግባቡ መከበር ከተጀመረ ወዲህ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተሻለ እና የሚያበረታታ ሥራ ለማከናወን ትጋት ማሳየታቸው የማይካድ ቢሆንም በሰላም ግንባታ፣ ተግባቦት፣ ዲሞክራሲን ከማዳበር አኳያ ዛሬም ብዙ እንደሚቀራቸ \ርንጉሴ ተፈራ በበኩላቸው ያነሳሉ፡፡

50 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በዲፕሎማሲ ሰራ ለይ ያገለገሉት አቶ ማዕረጉ በዛብህ ከምዕራቡ ዓለም የተኮረጀ እና የሀገሪቱን ህዝቦች ባህል፣ ትውፊት እና ስነ ልቦና ያላከበረ አሰራር ውስጥ መዘፈቅ እንደ ቀላል መታለፍ ያለበት ጉዳይ እይደለም ይላሉ፡፡ "የሌሎች ባህል ናፋቂነት በሚዲያዎች ይታያል"ሲሉም ይገልፃሉ፡፡

የሸገር ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ መዓዛ ብሩ የበኩላቸውን ሲናገሩ አሁን ላይ ያሉ ብዙ የፖለቲካ አንቂዎች ሚዲያው እንዲሆን የሚፈልጉት እና የሚዘውሩበት ሪዮት አለማዊ ሃሳብ ከገለልተኝነት መርህ አንፃር ምን ያክል ያራምድናል የሚለውን ጥያቄ ማጤን ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

19 ዓመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሆና ያገለገሉት እና አሁን ላይ በኮሚኒቲ ዲቨለፕመንት ስራ ላይ የተሰማሩት | አባይነሽ ብሩ የመገናኛ ብዙኃን የቋንቋ አጠቃቀም የማህበረሰብን ክብር ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ ለማሻሻል ጥረት አለመደረጉ የሚያሳዝን ነው ሲሉ ይገልፃሉ፡፡

service

 

አገልግሎት

ema
ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ema
ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

ema
የአቅም ግንባታ መስጠት

ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት

ema
ጥናቶችን መሰራት

የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት

Asset Publisher

ዜናዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ  ሪፖርት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ  የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ሀገራዊ ሪፖርት  ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በምግብ እና መድሃኒት ማስታወቂያዎች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር  ተወያየ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከምግብና መድሐኒት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በምግብ እና መድኃኒት ማስታወቂያዎች ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ዕርሰ ጉዳይ  ከመገናኛ ብዙኃን፣ከማስታወቂያ ድርጅቶች  ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሲሰጥ የነበረዉ በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ ሰልጣኞች በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ በሁለት ክፍል ሲሰጥ የነበረዉ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቋል።

pricestyle

getintouch

ማንኛውንም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ

broadcaster

 

በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ ብሮድካስተሮች በቁጥር

20
የህዝብ መገናኛ ብዙኃን
38
የንግድ ብሮድካስተር
56
የማህበረሰብ ብሮድካስተር
3
ሰብስክሪብሽን