ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ታህሳስ 15 2014 ዓ.ም
ኢ.መ.ብ.ባ ከ UN Women ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ ስለፆታ እኩልነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና የማስታወቂያ ባለሙያዎች በሚዲያ የሚያስተላልፏቸው ማስታወቂያዎች የሴቶችን ክብር የማይነኩና ሁለቱንም ፆታ ያማከለ ስራ መስራት እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ኢ.መ.ብ.ባ በማስታወቂያው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ከስርዓተ-ፆታ ጋር በተያያዘ ሴቶችን ዝቅ የሚያደርጉ ማስታወቂያዎች በበይነ-መረብ እና በየአካባቢው በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች በብዛት እናያለን። ስለሆነም ችግሩን ለመቅረፍ ብዙ መስራት ይጠብቀናል ብለዋል።
ስልጠናው ለሶስት ቀን የቆየ ሲሆን ተሳታፊዎቹ በስርዓተ ፆታ ምላሽ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ
ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት
የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት
ባለሥልጣኑ ከ UN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡:
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ ማስታዎቂያዎችን በተመለከተ በቅንጅት ለመስራት ነው።