ራዕይ

ራዕይ

  • 2022 የሕግ የበላይነትን እና የሙያ ስነ-ምግባርን ያከበረ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ እውን ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ

  • በአስቻይ ቁጥጥር፣ አቅም ግንባታ እና አጋርነት ብዝኃነቱ የተረጋገጠ እና በኃላፊነት የሚሰራ የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ዘርፍ ማጎልበት፤

እሴት

  • ገለልተኝነት
  • ተጠያቂነት
  • ትብብር
  • የሙያ ልህቀት

Asset Publisher

null የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከ UN Women ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በማስታወቂያ ዘርፉ የተሰማሩ የተለያዩ ባለሙያዎችን አሰለጠነ።

 

ታህሳስ 15 2014 .

... UN Women ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ ስለፆታ እኩልነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና የማስታወቂያ ባለሙያዎች በሚዲያ የሚያስተላልፏቸው ማስታወቂያዎች የሴቶችን ክብር የማይነኩና ሁለቱንም ፆታ ያማከለ ስራ መስራት እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን /ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ... በማስታወቂያው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ከስርዓተ-ፆታ ጋር በተያያዘ ሴቶችን ዝቅ የሚያደርጉ ማስታወቂያዎች  በበይነ-መረብ እና በየአካባቢው በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች በብዛት እናያለን። ስለሆነም ችግሩን ለመቅረፍ ብዙ መስራት  ይጠብቀናል ብለዋል።

ስልጠናው ለሶስት ቀን የቆየ ሲሆን ተሳታፊዎቹ  በስርዓተ ፆታ ምላሽ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።