የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፋይናስ ደህንንት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ህዳር 17 2014ዓ.ም
ስምምነቱን የተፈራረሙት በመገናኛ ብዙኃን ፋይናስ ደህንነትና ተያየዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ነው፡፡ በመገናኛ ብዙኃን ፋይናስ ደህንንትና ተያየዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ በኢትዮጵያ ግልፅ የመገናኛ ብዙኃን የፋይናስ አሰራር እንዲኖር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን የተቋማቱ ዋና ዳይሬክተሮች ገልፀዋል፡፡
በተለይም እየተስፋፋ ከመጣው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን እና ማስታወቂያ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሀገር ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ማረጋገጥን ጨምሮ በአጠቃላይ በዘርፉ የፋይናንስ ደህንነትን ማስጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትና የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጋራ ለመስራት ስምምነት ፈፅመዋል፡፡