ناشر الأصول

null የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋፅኦ  እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋፅኦ  እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ  "ክህሎት ለሁለንተናዊ ስኬት" በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ተጠቆመ፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፋሪያት ከማል እንዳሉት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግን ዘርፉ እንደ አማራጭ የትምህርትና ሥልጠና ስርዓት ሳይሆን በቀለም ትምህርት መግፋት ያልቻሉ ብቻ የሚገቡበት ሆኖ ይታያል፡፡  በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ዘርፉ አማራጭ ያጡ ሳይሆን መርጠው የሚገቡበት መስክ እንዲሆን መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን የለውጥ ሀሳብ በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ የሚቻለው ደግሞ በመገናኛ ብዙኃን በኩል በመሆኑ ለሚዲያ አመራርና ባለሙያዎች ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓቱ ላይ ያሉ መሰረታዊ የለውጥ አቅጣጫዎችና ከሀገራዊ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ጋር ያላቸው አንድምታ ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ስለቴክኒክና ሙያ ስልጠና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ የሚቀይሩና የባህሪ ለውጥ የሚያመጡ ዜናና ፕሮግራዎችን አቅደው በመስራት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ሚኒስትሯ ጨምረው ተናግረዋል።

በመድረኩ አስተያየት የሰጡ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ባገኙት ግንዛቤ ተመስርተው በዜናና ፕሮግራሞቻቸው ላይ በማካተት ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዎል።

መድረኩን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢኒስቲትዩት፣ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  እና ከዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር መዘጋጀቱ ተመላክቷል።

service

 

አገልግሎት

ema
ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ema
ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

ema
የአቅም ግንባታ መስጠት

ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት

ema
ጥናቶችን መሰራት

የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት

ناشر الأصول

ዜናዎች

የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ሚናቸው  የጎላ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አደረጉ

የቀድሞው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ አዲስ ለተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

pricestyle

getintouch

ማንኛውንም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ

broadcaster

 

በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ ብሮድካስተሮች በቁጥር

20
የህዝብ መገናኛ ብዙኃን
38
የንግድ ብሮድካስተር
56
የማህበረሰብ ብሮድካስተር
3
ሰብስክሪብሽን