ማስታወቂያ ለሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሙሉ

   ማስታወቂያ ለሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሙሉ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን በለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁ.1238/2013 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3/ለ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡ 

ስለሆነም ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት እና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት እናሳውቃለን፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0115-53-87-55/56 በመደወል ወይም በአካል ፍላሚንጎ አካባቢ ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

ብቁ መገናኛ ብዙኃን ለማህበረሰባዊ ንቃት!

የኢትዮዽያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን