ለሀገር ጠንቅ የሆኑትን የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ለሀገር ጠንቅ የሆኑትን የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

ለሀገር አና ለሰላም ጠንቅ የሆኑትን የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል  በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናገሩ።

ባለሥልጣኑ ከፍትህ አካላት እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ እና  በጋራ በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች አብሮነትን የሚሸረሽሩና ሰብዓዊነትን የሚያጎድፉ እንዲሁም ለሀገርና ለሰላም ጠንቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም የሃሳብ ነፃነትን በኃላፊነት የማይወጡ እና የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ልንከላከላቸው ይገባል ብለዋል።

አቶ መሐመድ አክለውም ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ስርጭትን በመከላከል ረገድ ሁሉም በያገባኛል ስሜት የየራሱን ኃላፊነት ወስዶ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን /ዋና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በበኩላቸው ዜጎች ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በአግባቡ ባለመጠቀም የሚፈጠሩ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል በህጉ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ በማወቅና መሻሻል ያለበትንም በማሻሻል በትብብር በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው በትብብርና በቅንጅት ባለመስራታችን ነው። በመሆኑም የመከላከሉን ስራ ለአንድ ተቋም ብቻ መተው ሳይሆን ሁላችንም ተናበንና ተቀናጅተን የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።