የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና ሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ ሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና ሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ ሰጠ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰልጣኞች በመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች፣ በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች እና በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ዙሪያ በድሬዳዋ ከተማ ሰልጠና ሰጥቷል፡፡

በሰልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር /ቤት ኃላፊ / የሽወርቅ ግርማ ሰልጣኞች በመሰረታዊ ጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆዎች፣ በሃቅ ማጣሪያ መንገዶች ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ እና ኃላፊነትን የተላበሰ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት በማዳበር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ  ራሳቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከተዛቡ መረጃዎች እንዲጠብቁ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

/ የሽወርቅ አክለውም የሚዲያ ኮሙኒኬሽን የቴክኖሎጂ እድገት ለማንኛውም የስራ ሂደት መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋፅኦ ቢኖረውም በአግባቡ ካልተጠቀሙበት ለጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት መስፋፋት ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ዜጎች ቴክኖሎጂን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ገልፀው በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት  ለሌሎች ማካፍል እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

የድሬዳዋ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ እቶ ሱሌማን አሊፋራህ  በበኩላቸው የጋዜጠኝነት ሙያ በአግባቡ ከተጠቀሙበት ሀገርን የሚያለማ፣ ማህበረሰቡን በመረጃ የሚያበለፅግ ነው። ሙያውን በአግባቡ ካልተጠቀምን ደግሞ ማህበረሰቡን እርስበርስ በማቃቃር፣ ለሠላም መደፍረስ ዋነኛው ምክንያት በመሆን ሀገር የማፍረስ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ሙያውን በከፍተኛ ጥንቃቄ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው በጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር እና መርሆች እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም እና ሃቅ ማጣሪያ መንገዶች  ዙሪያ  ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት ተሳታፊ በመሆንና ጥቆማ በመስጠት ከባለሥልጣኑ እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ስልጠናዉን ለተካፈሉ ሰልጣኞች ስርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የዜጎችን ተሳትፎ እና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት /Media literacy/ የሚያሳድጉ ዘዴዎችን ቀይሶ ዜጎች ራሳቸዉን፣ ቤተሰባቸዉን ብሎም ሀገራቸዉን ከሐሰተኛ መረጃ እንዲከላከሉ ለማስቻል የሚያግዙ ስልጠናዎችን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡