Publicador de continguts
ታህሳስ 15 2014 ዓ.ም
ኢ.መ.ብ.ባ ከ UN Women ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ ስለፆታ እኩልነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና የማስታወቂያ ባለሙያዎች በሚዲያ የሚያስተላልፏቸው ማስታወቂያዎች የሴቶችን ክብር የማይነኩና ሁለቱንም ፆታ ያማከለ ስራ መስራት እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ኢ.መ.ብ.ባ በማስታወቂያው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ከስርዓተ-ፆታ ጋር በተያያዘ ሴቶችን ዝቅ የሚያደርጉ ማስታወቂያዎች በበይነ-መረብ እና በየአካባቢው በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች በብዛት እናያለን። ስለሆነም ችግሩን ለመቅረፍ ብዙ መስራት ይጠብቀናል ብለዋል።
ስልጠናው ለሶስት ቀን የቆየ ሲሆን ተሳታፊዎቹ በስርዓተ ፆታ ምላሽ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።