ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ "ክህሎት ለሁለንተናዊ ስኬት" በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ተጠቆመ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፋሪያት ከማል እንዳሉት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግን ዘርፉ እንደ አማራጭ የትምህርትና ሥልጠና ስርዓት ሳይሆን በቀለም ትምህርት መግፋት ያልቻሉ ብቻ የሚገቡበት ሆኖ ይታያል፡፡ በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ዘርፉ አማራጭ ያጡ ሳይሆን መርጠው የሚገቡበት መስክ እንዲሆን መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን የለውጥ ሀሳብ በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ የሚቻለው ደግሞ በመገናኛ ብዙኃን በኩል በመሆኑ ለሚዲያ አመራርና ባለሙያዎች ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
መገናኛ ብዙኃን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓቱ ላይ ያሉ መሰረታዊ የለውጥ አቅጣጫዎችና ከሀገራዊ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ጋር ያላቸው አንድምታ ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ስለቴክኒክና ሙያ ስልጠና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ የሚቀይሩና የባህሪ ለውጥ የሚያመጡ ዜናና ፕሮግራዎችን አቅደው በመስራት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ሚኒስትሯ ጨምረው ተናግረዋል።
በመድረኩ አስተያየት የሰጡ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ባገኙት ግንዛቤ ተመስርተው በዜናና ፕሮግራሞቻቸው ላይ በማካተት ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዎል።
መድረኩን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢኒስቲትዩት፣ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ከዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር መዘጋጀቱ ተመላክቷል።
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ
ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት
የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ አዲስ ለተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።