“ከጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የፀዳች ሀገር ለመፍጠር የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል” አቶ መሐመድ እድሪስ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (IMS) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አባላት መምህራንና ተማሪዎች በጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ መከላከያ መንገዶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡