Tartalom megjelenítő

null የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ጋር ውይይት አካሄደ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 2014 (...)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩ ዓላማ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸው ይዘቶች በሀገራችን ተከብሮ የቆየውን የሃይማኖት መቻቻልና አብሮነት ለማጠናከር እንዲሁም በሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን  ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ  እንዳሉት የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ግብረ ገብነትን በማስተማር ትውልድን ከማነፅ በተጨማሪ የጋራ እሴቶች እንዲጠናከሩ፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት እንዲጎለብት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ስለሆነም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን በአስተምሮታቸው አሁን ላለንበት ችግር መፍትሄ በሚያመጣ ሀገር በሚገነባና መልካም ዜጋን በሚያንፅ  ጉዳይ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የአብሮነት አሴቶችን በማጠናከር እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ሊጫወቱት ስለሚገባው ሚና እንዲሁም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የህግ ማዕቀፎች የሚሉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለምዝገባ የሚየስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን   አሟልተው ምዝገባ ላከናወኑ 23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ሰርተፊኬት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ውይይቱ ተጠናቋል።

service

 

አገልግሎት

ema
ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት

ema
ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ

ema
የአቅም ግንባታ መስጠት

ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት

ema
ጥናቶችን መሰራት

የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት

Tartalom megjelenítő

ዜናዎች

የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ሚናቸው  የጎላ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አደረጉ

የቀድሞው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ አዲስ ለተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

pricestyle

getintouch

ማንኛውንም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ለማቅረብ

broadcaster

 

በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ ብሮድካስተሮች በቁጥር

20
የህዝብ መገናኛ ብዙኃን
38
የንግድ ብሮድካስተር
56
የማህበረሰብ ብሮድካስተር
3
ሰብስክሪብሽን