የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የ6ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የ6ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ባለፋት 6ወራት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተቋሙን ለማሳደግ ሁሉም የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል። በተለይም የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን ከመከላከል ረገድ በመደበኛነት የመገናኛ ብዙኃንን ክትትል ከምናደርገው በተጨማሪ የሁሉንም ሰራተኞች ተሳታፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ሰራተኞች ክትትልና የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ሰራተኞች በዕውቀት እና በሌሎች አስፈላጊ በሆኑ የህይወት ክህሎቶች እራሳቸውን በማብቃት ተቋሙ ቀጣይ በሚኖሩት የስራ ጊዜያት ውስጥ ብቁ ሰራተኛ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የባለሥልጣኑ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉ ሁሉም ሰራተኞች የተቋሙን የስራ አፈፃፀም ተረድተው በጥንካሬ የተያዙትን ለማስቀጠል እና ክፍተት የታየባቸውን ደግሞ ወደፊት ለማሻሻል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።