የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በምግብ እና መድሃኒት ማስታወቂያዎች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በምግብ እና መድሃኒት ማስታወቂያዎች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከምግብና መድሐኒት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በምግብ እና መድኃኒት ማስታወቂያዎች ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ዕርሰ ጉዳይ ከመገናኛ ብዙኃን፣ከማስታወቂያ ድርጅቶች ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የማስታወቂያ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዮናስ ፋንታዬ እንዳሉት የውይይቱ ዓላማ መገናኛ ብዙኃን ምግብ እና መድኃኒት ነክ የሆኑ ማስታወቃያዎችን ሃላፊነትን ተላብሰዉ እንዲያሰራጩ ለማስቻል እንዲሁም ዘርፉ በህግና ስርዓት እንዲመራ በሚደረገው ጥረት መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ ነው።
አቶ ዮናስ አክለውም በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ የመድኃኒት፣ የምግብና መጠጥ የመሳሰሉ ማስታወቂያዎች በህግና ስርዓት እንዲመሩ ማስቻል ማህበረሰቡን ካልተገባ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንግልት መጠበቅ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸው በምግብና መድኃኒት ምርቶች ዙሪያ የሚሰራጩ ማስታወቂያዎች ህግ እና ስርዓትን የተከተሉ መሆን አለባቸው፡፡ስለሆነም ማስታወቂያ በህግና ስርዓት እንዲመራ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ሚና ከፍተኛ ነው ፡፡ስለዚህ ሁላችንም ተባብረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የምግብ ማስተዋወቅ መመሪያ አተገባበርና ነባራዊ ሁኔታዎችና የሚዲያ ሚና እንዲሁም ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።