ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
ባለሥልጣኑ ለሰራተኞቹ ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሚዲያ ሬጉላቶሪ ተልዕኮ የሚመጥን ተቋማዊ የስራ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንዳሉት የሥልጠናው ዓላማ ሁሉም የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ጥሩ የስራ ባህልን እንዲገነቡ ለማስቻል እና ለስራ እንዲነሳሱ እንዲሁም ብቁ ሰራተኞች ሆነው ሀገርን እንዲያገለግሉ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።
አቶ መሐመድ አክለውም የምትወስዱት ስልጠና አስተማሪና ተነሳሽነትን የሚፈጥር በመሆኑ በተግባር በመቀየር ልትጠቀሙበት ይገባል ሲሉ ለሰራተኞቹ አሳስበዋል፡፡
ለብሮድካስት፣ ለበይነ መረብ እና ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት
የመገናኛ ብዙኃን እና የማስታወቂያ ይዘት ክትትልና እና ቁጥጥር ማድረግ
ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማስታወቂያ ዘርፍ የአቅም ግንባታ መስጠት
የዘርፉን እድገት እና ለውጥ ለማጠናከር የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሰራት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ አዲስ ለተሾሙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።