"መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ሰላም እና ለህዝብ አብሮነት መጠናከር ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይገባል" አቶ መሐመድ እድሪስ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ሰላም እና ለህዝብ አብሮነት መጠናከር ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይገባል" አቶ መሐመድ እድሪስ

መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ሰላም እና ለህዝብ አብሮነት መጠናከር ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ተናገሩ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች እና የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የለውጥ ስራዎችን በጎበኙበት እና የልምድ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም መገናኛ ብዙኃን ሰላም እንዲሰፍን እና አብሮነት እንዲጠናከር የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ወቅታዊ እና የጠራ መረጃ በማድረስ ለሰላም እና ለአብሮነት መጠናከር ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች እና የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በባለለሥልጣኑ ባደረጉት ጉብኝት መደሰታቸውን ገልፀው የተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ልምድና ትምህርት የሚወሰድባቸው እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ማህበረሰቡ በተዛባ መረጃ እንዳይታለል ትክክለኛ መረጃ በማድረስ ለሀገር ሰላም እና አብሮነት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡