ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለ2ተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ 2ተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ 11 ዱም /ከተሞች ከሚገኙ 2ተኛ ደረጃ /ቤቶች ለተወጣጡ የሚኒ ሚዲያ ተማሪዎች   በጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ መከላከያ መንገዶች ዙሪያ  ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናውን የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንዳሉት የቴክኖሎጂ መስፋፋትን ተከትሎ በርካታ መገናኛ ብዙኃን እየተበራከቱ በመሆናቸው  በርካታ የተሳሳቱ፣ ሀገርን የሚያፈርሱ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሐሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ሲሰራጩ ይስተዋላሉ፡፡

ስለሆነም  ታዳጊዎች እነዚህን መገናኛ ብዙኃን ሲጠቀሙ  የትኛው መረጃ ትክክል እንደሆነ እና እንዳልሆነ እንዲሁም የትኛው መረጃ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ነው የሚለውን በመለየት እና ባለማሰራጨት፣ ባለማጋራት እንዲሁም ተሰራጭቶ ሲያገኙ ለባለሥልጣኑ በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የሚኒ ሚዲያ ተማሪዎችን በመገናኛ ብዙኃንና መረጃ አጠቃቀም ዙሪያ ማሠልጠን  አብዛኛው የወጣቱን ክፍል በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልፀው ተማሪዎቹ ከወዲሁ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ እንደሚያግዛቸውም ተናግረዋል፡፡  

ወጣቶች ነገ የሚረከቧት ሀገር ከጥላቻ የፀዳች እንድትሆን ጥላቻን በመፀየፍ የሀገርን አንድነትና የህዝቦችን አብሮነት ለማፅናት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ዛሬ ላይ መወጣት እንደሚኖርባቸውም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ይህ መድረክ የማስጀመሪያ ሲሆን ወደፊት በአዲስአበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 2ተኛ ደረጅ /ቤቶች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ 2 ደረጃ /ቤቶች   መሰል ስልጠናዎችን ባለሥልጣኑ ወደፊት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

ሰልጣኝ ተማሪዎች በበኩላቸው ስልጠናው ከማህበራዊ ሚዲያ እና ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የሚገኙ መረጃዎችን መረዳት እንድንችል እና የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ የሚያስከትለውን ጉዳት እንድንረዳ ግንዛቤ ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

ስልጠናው 11ዱም /ከተሞች ከሚገኙ /ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎች እና መምህራን የተሳተፉበት እና የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ምንነት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባህሪያት፣ እውነትን ማጣራት (fact-check) እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።

ተማሪዎቹ  ወደ /ቤታቸው ሲመለሱ በሚኒ ሚዲያ ተሳትፏቸው ውስጥ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጪያ ስራ እንዲሰሩ ያግዛቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።