የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ  ሪፖርት ይፋ አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ  ሪፖርት ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ  የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ሀገራዊ ሪፖርት  ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕከት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ባለሥልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት  የጥላቻ ንግግር  እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን በተመለከተ ሀገራዊ ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል፡፡ የዚህ ሪፖርት ዓላማም በማህበራዊ ሚዲያ  ላይ የጥላቻ ንግግር  እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚገኝበትን ሁኔታ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያሳየውን እድገትና አሉታዊ ተፅዕኖ በማመላከት የመፍትሄ ሀሳብ ለመጠቆም ያለመ ነው ብለዋል፡፡

/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን ስርጭትን የመከላከል ስራ ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት ሳይሆን የሁሉንም ተቋማት እና ግለሰቦች ትብብር የሚጠይቅ ስለሆነ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንዲሚገባ መልዕከትአስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጥላቻ ንግግር እና በሐሰተኛ መረጃ ስርጭት አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 4 በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት  የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ሀገረዊ  ሪፖርት ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ሃላፊነት የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡