资产发布器
5 ጥቅምት 2014 ዓ.ም.
አይ. ኤም. ኤስ. (IMS) ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋር የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በትብብር የሚሰራ አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ተቋሙ ከባለሥልጣኑ ስር ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ክትትል(የሞኒተሪንግ) ክፍሎች ጋር በመሆን የክትትል ስራን ለማሳደግ፣ ለማዘመን እና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪውን ለማብቃት ከባለሥልጣኑ ጋር እየሰሩ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንም ከአይ. ኤም. ኤስ. ጋር በመስራት በሞኒተሪንግ ስራ ብቃት ያላቸውን ሰራተኞች ለማብዛት እና ስራውን ስኬታማ ለማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥና በቀጣይ ከሞኒተሪንግ ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡