የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለፀ
የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ በሰላም ግንባታ ዙሪያ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በኃላፊነትና በአንድነት መንፈስ የሰላም ግንባታ ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
በመድረኩ የሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸው ሚና እና እየሰሩት ያለው ስራ ምን ይመስላል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።