የንግድ ኤፍ. ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

    የንግድ ኤፍ. ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት 

                         የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 30 በተሰጠው ሥልጣንና 
ተግባር መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም የሚፈልጉ አመልካቾችን አወዳድሮ 
ለ5 /አምስት/ አመልካቾች ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት:-
ፈቃድ ለመስጠት የታሰበው ብሮድካስት አገልግሎት ዓይነት፡- የኤፍ.ኤም ሬዲዮ፣
አገልግሎቱ የሚሸፍነው አካባቢ፡- አዲስ አበባ፣
ዝግጁ የሆኑት የሬዲዮ ሞገዶች፡- 92.5፣ 93.5፣ 94.5፣ 95.5 እና 96.5 (MHZ) ናቸው
የፈቃድ ሁኔታዎችና ግዴታዎች፡-
ማንኛውም ባለፈቃድ ፈቃዱን ለመውሰድ ባመለከተበት ወቅት በማመልከቻው የገለጻቸው እንዲሁምበአዋጅ ቁጥር 1238/2013
እና አዋጁን ተከትለው በሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መሰረት በፈቃዱ ውስጥ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች የፈቃዱ ግዴታዎች 
ሆነው ይቆጠራሉ፡፡
የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜና ቦታ፡-
በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት የ3 ወር ጊዜ
ውስጥ ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የፋይናንስ፣ ግዥ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት
ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር 101 ብር 50 (ሃምሣ ብር) በመክፈል የማመልከቻ ቅጽ ወስዳችሁ በመሙላት እና ለውድድሩ አስፈላጊ
የሆኑ ሰነዶችን ከማመልከቻ ቅጹ ጋር በማያያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች የፕሮጀክት ሰነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 3 ወር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የብሮድካስት ፈቃዱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 6 ዓመት ሲሆን የፈቃድ ዘመኑ ሲጠናቀቅ የሚታደስ ይሆናል፡፡
የማመልከቻና የፈቃድ ክፍያ መጠን፤- አመልካቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ሲወሰን የማመልከቻ ብር 500 እና የፈቃድ ብር 75,000 
(በድምሩ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ይከፍላል፡፡
የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በታተመ በ91ኛው ዕለት በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት 
ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
ባለሥልጣኑ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-53-87-55/56/65/66 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡