Asset Publisher

null የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ እየተከበረ ይገኛል፡፡ የዘርፉ ሙራን፣ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን በላስልጣን ከፍተኛ አመራሮች፣ የአለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ላይ ተገኝታዋል፡፡

በአከባበሩ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሃመድ እድሪስ እንዳሉት ሃገሪቱ በተግባር ያደረገችው የፖሊሲ እና የህግ ሪፎርም ለዘርፉ ማደግና መስፋፈት ብሎም የፕሬስ ነጻነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ እድል ቢሆንም አሁንም ቢሆን ሃላፊነት የጎደለው ጋዜጠኝነት የሚተገብሩ፣ በጎሳ ፍላጎት የሚነዱ፣ እና የሃገር ጥቅምን አሳልፈው የሚሰጡ ሚዲያዎች አሉ፡፡

ያለንበት ወቅት የፔሬስ ነጻትን ከሃላፊነት ጋር ባጣጣመ መልኩ መረጃን ማስተላለፍና ዜጎችን ከጥላቻ እና ከሃሰተኛ መረጃ መታደግ የሚጠይቅ ሲሆን ስድስተኛ ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና የተሳካ እንዲሆን ሚዛናዊ፣ ከስሜት የፀዳ፣ ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ አገራዊ ተልዕኮዋቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

በኮንፍርንሱ ላይ የውይይት ሃሳብ ያቀረቡ ሙሁራን እና የዘርፉ ባለሙያዎችም የዜጎች የመረጃ አወሳሰድ እና አቀባበል ላይ ግንዘቤ በመፍጠር ማህበረሰቡ እራሱን ከሃሰተኛ መርጃ መከላከል እንዲችል የሚያግዝ ስራ መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ከተሳታፎዎችም በኩል መንግስትጋ ያለ የመረጃ ተደራሽነት ችግር ሚዲያዎች በመረጃ እጥረት ምክንያት የሚያጠናቅሩት ዜና ጥራት የሌለው እና ሚዛናዊነት የጎደለው እንዲሆን ያደርጋል የሚል አስተያየት ተሰጥቷል፡ በመገናኛ ብዙኃን እና በጋዜጠኞች ስብስብ የተቋቋመው የጋራ ምክር ቤት የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር እንዲከበር ከማድረግ አንጻር የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የበይነ መረብ ሚዲያውም በሙሉ ነጻነት እንዲሰራ ከስፈለገ ግልጽ ወደ ሆነ አሰራር መምጣት አለበት ተብሏል፡፡ የመረጃ እውነትነተኝነትን የሚያረጋግጡ አካለት መበረታት አለባቸውም ተበሏል፡፡ የኮንፍረንሱ መዝጊያ ላይ ማጠቃለያ የሰጡት አቶ አማረ አረጋዊ በብዙ ሃገራት የማይቀለበስ ግጭት የሚከሰተው በልተረጋገጠ እና ሀሰተኛ መረጃ በመሆኑ ለህቡ የምንሰጠው መረጃ የስነ ምግባር መመሪያን ያከበረ እንዲሆን ቃል የምንገባበት ቀን መሆን አለበት ብለዏል፡፡

ትናንሽ ችግሮቻችንን ትልቅ፣ ትላልቅ ጉዳዮቻችንን ትንሽ የማድረግ አላማ ይዘው የሀሰተኛ መረጃ አሰራጮችን የምንታገልበት የጋራ ሚና ሊኖር ይገባል፤ ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላት ሀገር እንድትሆን ሁላችንም መረባረብ አለብን ሲሉም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣነ ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡