የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከግል መገናኛ ብዙኃን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዉና ነበራዊ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢንተርኮንቲንነታል ሆቴል ባዘጋጀው መድረክ ላይ የተለያዪ የግል መገናኛ ብዙኃን ባለቤቶች፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሮችና የመከላከያ ኔራሎችተግኝተው ነበር፡፡

የመድረኩ አላማ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ እና በሃገር ጥቅም ማስከበር ዙሪያ የተቋማት የጋራ ሚና ምን መምሰል እንዳለበት ከንግድ መገናኛ ብዙኃን ጋር ለመምከር ነር፡፡በምክክሩ ላይ የተገኙት ጄኔራሎች፣ አምባሳደሮችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች የሃገሪቱ ነበራዊ ሁኔታን በተመለከተ በየበኩላቸው ያለውን እውነታ አብራርተዋል፡፡

አምባሰደር ፍሰሐ ሻዎል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሲሆኑ በዲፕሎማሲው አለም የረጅም ግዜ ልምድ ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ አምባሳደሩ ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ማብራሪያ ሲሰጡ የውጭ ሚዲያዎችን እና አለም አቀፍ ተቋማትን እንደመሳሪያ በመጠቀም እየተፈጠረ ያለው የውጭ ጫና  ከሃላያላኑ ሃገራት ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎት ጋራ በቀጥታ የሚገናኝ ነው፡፡

አሸባሪው የህውሐት ሃይል የሚፈፅመውን ግፍ እና መከራ በገሃድ እየተመለከቱ  አይናቸውን ለመጨፈንና ለምንነግራቸው እውነት ጆሮ ዳባ ለማለት የመረጡት የውጭ ሃይሎች ከራሳቸው ፍላጎት አንፃር ኢትዮጵያ የያዘችው ጉዞ በፍፁም አልጣማቸውም፡፡ እንደ አምባሳደሩ ምልከታ የሃገሪቱ አካሄድ እነሱ አለምን በሚቆጣጠሩበት ስትራቴጂክ የጂኦ ፖለቲካዊ ቀመር ውስጥ የማይፈለግ የድምር ውጤት ይዞባቸው መጥቷል፡፡ “የሃላኑ ሃገራት ታሪካዊ ቀመር ምንድ ነው? አለምን ለመቆጣጠር፣ ግብጽን መቆጣጠር፣ ግብፅን ለመቆጣጣር አባይን መቆጣጠር፣ አባይን ለመቆጣጠር ደግሞ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ነው”

ስለሆነም ይላሉ አምባሳደሩ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ በውጭ ሚዲያዎች እና አለም አቀፍ ተቋማት በኩል የሚጮሁ ሃገራት ስለኛ መልካም እጣ ፈንታ ተጨንቀው ሳይሆን ይህን ስታራቴጂክ ፍላጎት የሚያሳካላቸውን ወዳጅ ነፍስ መልሶ ለመዝራትና ጉልበቱን ለማፈርጠም ነው፡፡

አምባሳደር ፍሰሐ ይላሉ፣ “ብዙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ወደ ሃገር ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህን ሃይሎች ሃያላኑ ለመጠቀም አልቻሉም፡፡ ሁሉንም ሲመለከቷቸው በሃገር ብሔራዊ ጥቅም እና ሉዓላዊነት አንደራደርም ብለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአንድነት ቆመዋል፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ላይ ቦክስ ሊሰነዝርላቸው የሚችል አንድ ሃይል ቢኖር ህውሓት ብቻ ነው፡፡ የነሱ ፍላጎት ማንኛውንም ድጋፍ አድርገውለት እንደ ቀድሞ ታሪኩ በአማራ በኩል አድርጎ ወደ አዲስ አባባ እና አራት ኪሎ እንዲገባ ነው”

በአባይ የውሃ ዲሞፕሎማሲ ላይ የራሳቸው ምክንያት እና አመክንዮ ጠልፎ የጣላቸው ግብፅ እና ሱዳን የሚገቡበት አመቺ ሀኔታ አለመፈጠሩ ከዚህ ሃይል ጎን ናቸው፡፡

“ያም ሆኖ በሱዳን ውስጥ የምንመለከተው የህውሐት ሃይሎች ትርዒት አለ፡፡ ግብፅ ከሱዳን ባለፈ ደቡብ ሱዳንን እና ሶማሊያን እየዞረች “እየፈረሰች ካለች አገር ጋር ከምትሆኑ ከኛ ጋር ብትሆኑ አይሻላችሁም ወይ?” እንደምትላቸው ቀደም ብለን መልካም የሰራንላቸውና ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የፈጠርባቸው ሃገራት ስለሆኑ ይነግሩናል”

ስለዚህ ይላሉ አምባሳደሩ ለግል መገናኛ ብዙኃን ሃላፊዎች ሲያብራሩ፣ የውጭ ሃይሎችን ርብርብ በዚህ ልክ መረዳትና በቴሌቪዥን፣በሬዲዮ እና በማበራዊ ድረገፆች ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን ለብሔራዊ ጥቅም እና እንድነት ፋይዳ በሚሰጥ መልኩ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡

አቶ መሐመድ ኢድሪስ ሃገር ችግር ውስጥ ባለችበት ሰዓት ለህዝብ ጥቅም ያለመቆም ጉዳይ የሚታየው በመረጃ ዘገባ ወቅጥ በሚታይ ጥሰት ወይም ተግባር (Commsion) ብቻ ሳይሆን ተገቢውን የማህበረሰብ ወገንተኝነት ሳያሳዩ በመቅረትም (ommsion) ጭምር ነው፡፡

ሃገርን ለማዳን ተልዕኮ ወስዶ መስራት ለህዝብ ያለን ወገንተኝነት ማሳየት ነው፡፡ይህ ግዜ ወገንተኝነታችንን የምናሳይበት ሰዓት ነው፡፡ ስሙ የግል ይሁን እንጂ ሚዲያ የህዝብ ሃብት መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ የህብረተሰብን  ስነ-ልቦና ከጥቃት መከላከል ከናንተ የሚጠበቅ ነው” ሲሉ አቶ መሐመድ ያብራራሉ፡፡

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ብርጋዴር ጌኔራል ቡልቱ ታደሰ  በበኩላቸው የህውሓትን መሰረታዊ ሀገር ጠልነት እና የክፋት ልክ ተረድቶ የውጭ ሚዲያዎች ሃሰትን በሚያሰረጩበት ልክ ሃገርን ከጥፋት ለማዳን የሚያስችል የህዝብ ወገንተኝነትን የሚያሳይ ስራ ከግል መገናኛ ብዙኃን ይጠበቃል ሲሉ ይናገራሉ፡፡

በዚሁ  ሃሳብ ላይ አክለው የመከላከያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ኮሮኔል ጌትነት አዳነ እንዲህ ይላሉ የውጭ ሚዲያዎች የትግራይ መከለከያ ሰራዊት ወይም ሃይል (Tigray Defence Force) ብለው በተደጋጋሚ የሚፅፉት የአንድ ክልል ሃይል እና አሸባሪ መሆኑ ጠፈቷቸው አይደለም፡፡ እነሱ ይህን ካደረጉ እኛ ሃገር ውስጥ ላለነው የደመራው እንጨት ወዴት ሊወድቅ ይችላል የሚል መሐል ሰፋሪነት አያስፈልግም፡፡ የሚወድቀው ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ፈር ቀዳጅ እንዲሆን ያለምንም መጠራጠር ለኢትዮጵያ መስራት ግን  የሁላችንም ሃላፊነት ነው