የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር አና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚከታተልበትን የጥሪ ማዕከል ገንብቶ ስራ ላይ አዋለ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከታተል የሚያስችለውን የቅሬታና እና ጥቆማ መቀበያ የጥሪ ማዕከል ገንብቶ ስራ ጀምሯል፡፡

በቅርቡ የተገነባው የጥሪ ማዕከል ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግርን እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ እና የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለማስፈፀም የሚያግዝ ነው፡፡

የጥሪ ማዕከሉ 9192 ነጻ የስልክ መስመር የሚጠቀም ሲሆን ዜጎች በተለያዩ መደበኛ እና የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚተላለፍ ማንኛውም ይዘትን በተመለከተ የሚያቀርቡትን ጥቆማ፣ አስተያየት አና ቅሬታ መቀበያና ማስተናገጃ ነው፡፡

ጥሪ ማዕከሉ በ9 ባለሙያዎች የተደራጀ ሲሆን ዘወትር በስራ ሰዓት ጥሪዎችን እየተቀበለ እና እያስተናገደ ይገኛል፡፡ባለሥልጣኑ ማንኛውም ሰው በሬዲዮና በቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ በጋዜጣ፤ በመፅሄት፤ በበይነ መረ መገናኛ ብዙኃን ላይ ቅሬታ ወይም ጥቆማ ካለው ለባለሥልጣኑ ሲያቀርብ ውሳኔ ማግኘት የሚችልበት አሠራር ተዘርግቷል፡፡

ቅሬታ ማለት በሚተላለፉ ዜናዎች፥ ፕሮግራሞችና ማስታወቂያዎች ላይ መብቴ ተነከቷል ወይም በአግባቡ አልተስተናገድኩም በማለት በብሮድካስተሮች ላይ የሚቀርብ አቤቱታ ሲሆን ጥቆማ ማለት ደግሞ በማናቸውም በተላለፉ ዜናዎች፥ ፕሮግራሞችና ማስታወቂያዎች ላይ ማስተካከያ ወይም እርምት እንዲደረግ ለባለስልጣኑ የሚቀርብ መረጃ የሚሰጥ አስተያየት ነው፡፡