የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተቋሙ የ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ህዳር 04 2014 ዓ.ም.

በውይይቱ የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በእቅድ የተያዙ ስራዎች አፈጻጸማቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች እና የተስተዋሉ ክፍተቶች በሪፖርቱ ተነስተዋል። ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ደግሞ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት እንዴት ማሻሻል እንደሚገባ እና ወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የስነ-ምግባር ደንብ ማሻሻያ ዙሪያ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲሁም ጥሩ ስነ-ምግባር የተላበሡ ሠራተኞችን በመፍጠር ተጨባጭ ስራ ለመስራት ባለሥልጣኑ የራሱን የስነ-ምግባር ደንብ ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን በዚህ ርዕስ ዙሪያ ለሠራተኞቹ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በመቀጠልም የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በሩብ ዓመቱ የስራ አፈፃፀም ውይይት ላይ በተነሱ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች ዙሪያ ከሠራተኞቹ ግብዓት በማሰባሰብ እያወያዩ ይገኛሉ። በውይይቱም ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተነሱ ጠንካራ ጎኖች የሚበረታቱና መቀጠል ያለባቸው ሲሆን ያሉትን ክፍተቶች ደግሞ ከውይይቱ ያገኘነውን ግብዓት ጨምረን ወደፊት የተሻለ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።