የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ኦን ፕሮሞሽን ኃ/የተ/የግ/ማ (On promotion PLC) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው አለም አቀፉ የሚዲያ ኤክስፖ በጋራ ለማዘጋጀት በዛሬው እለት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ህዳር 10 2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ኤክስፖዎች በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳሉ፤ በሀገራችን ደረጃም አሁን መጀመሩ ለሚዲያው እድገት ትልቅ እምርታ ነው። ስለሆነም ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

ኤክስፖው የሚካሄደው ሰኔ ወር 2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ሲሆን ዋና አላማው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙኃን የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ መድረክ ለማመቻቸት ሲሆን በእለቱም ከ80 በላይ የሚሆኑ የሚዲያ አካላት እና ከ500 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተው የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ።

ይህንን ዝግጅት አለም አቀፋዊ ይዘቱንና ጥራቱን የጠበቀ አድርጎ ለማዘጋጀት ከባለሥልጣኑ በተጨማሪም ኦን ፕሮሞሽን ቤዚክ ሊድ (Basic Lead) ከሚባል መቀመጫውን ሎስ አንጀለስ ካደረገ ድርጅት ጋር እየሰራ ይገኛል። Basic Lead በቅርቡም በታህሳስ ወር በሩዋንዳ ኪጋሊ በሚያዘጋጀው ዲስኮፕ አፍሪካ የሚዲያ ኤክስፖ (DISCOP Africa Media Expo) ላይ ኢትዮጵያ እንደምትሳተፍ ተገልጿል።