የኢ. መ.ብ.ባ የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል፡፤

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ውይይቱ ባለፉት 9 ወራት በባለሥልጣኑ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል እና ከዕቅድ በታች የተተገበሩ ስራዎችን በምን መልኩ ማሻሻል እንደሚቻል ለመወያየት ያለመ ነው።

 

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከእቅድ አኳያ የተሻለ አፈፃፀም እንዳለ ገልፀው በታዩ ክፍተቶች ላይም ወደፊት ማሻሻል እንደሚያስፈልግ እና ጥናትና ምርምር ላይ በማተኮር የሚዲያ ኢንደስትሪውን ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በተቋሙ በቴክኖሎጂ የታገዘና በአቅም ግንባታ የዳበረ የሰው ሃይል እንዲኖር መስራት አለብን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል።