ባለሥልጣኑ ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

አዳማ፣መጋቢት 17/2015 . (...)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች፣ በሙያ ስነ-ምግባር መርሆች እና በማህበረሰብ ብሮድካስት ሚና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡

የስልጠና መድረኩን የከፈቱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ላይ የሚሰሩ ስራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አቅም ያላቸው በመሆኑ ባለሥልጣኑ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራዎችን ይሰራል ብለዋል፡፡

የጀሰቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ /ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ገዛኸኝ በበኩላቸው ድርጅታቸው ከባላሥልጣኑ ጋር በመተባበር ለመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እየሰጠ ያለውን የአቅም ግንባታ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ 

በመድረኩ ላይ በዋናነት የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ፣ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ እንዲሁም የህፃናት ፕሮግራም የይዘት ዝግጅትና አቀራረብ  ማንዋል ላይ በባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም በስልጠናው ላይ የማህበረሰብ ብሮድካስት አስተዋጽዖ እና በባለስሥልጣኑ የክትትል አግባብ በተለዩ ከአደረጃጀት፣ ከይዘት ዝግጅት፣ ከቴክኒክ መሳሪያዎች፣ ከገቢ፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲሁም ከአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በዝርዝር ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

 

 

እስካሁን ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ከወሰዱ 59 የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች  መካከል 7  በተለያዩ ምክንያቶች ስርጭት ያቋረጡ፣ 28 በስርጭት ላይ ያሉ ሲሆን 24 ደግሞ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡