ባለሥልጣኑ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

 

በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንዳሉት የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት ባለሥልጣኑ ጊዜን፣ ገንዘብን እና ጉልበትን በመቆጠብ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለዜጎች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት በእጅጉ ያግዘዋል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በቀጣይ ባለሥልጣኑ የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጡን በጥብቅ ዲስፕሊን በመምራት የዜጎች የአገልግሎት እርካታን ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ባለፉት አራት ዓመታት ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ሰፊ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የዓለም አቀፉን የጉምሩክ አሰራር ስርዓት የተከተለ የአገልግሎት ስታንዳርድ ለማስፈን እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንሚቀጥልም ኮሚሽነሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት ምንነትና አስፈላጊነትን በተመለከተ አቶ ሮቤል ተስፋዬ የኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት ፕሮጀክት /ቤት ስራ አስኪያጅ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት በርካታ ተቋማትን ወደ ስርዓቱ በማስገባት ደንበኞች ከጊዜ፣ ከገንዘብና ከድካም አንፃር ይፈጠርባቸው የነበረውን ጫና ማቃለል መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮሚሽኑ ጋር ተመሳሳይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡