የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ UN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

 

የውይይቱ ዋና ዓላማ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከግጭት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዘገባዎች በሚዘግቡበት ጊዜ ስርዓተ ፆታ ላይ የተመረኮዙ ጅምላ ፍረጃዎችን፣ የተዛቡ ስርዓተ ፆታዊ አስተሳሰቦችን እና አድሎዎችን እንዲያስወግዱ እንዲሁም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የግጭት ዘገባ አቀራርቦችን እንዲገነዘቡ እና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ እንደተናገሩት የፆታ እኩልነት የወንዶችና ሴቶችን ድምፅ በእኩል መጠን ለማስተናገድ እንዲያመች ስርዓተ-ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ተዘጋጅቷል። በመሆኑም ይሄን ለማስፈፀም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም አሳስበዋል።