የኢ.መ.ብ.ባ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢ.መ.ብ.ባ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ስልጠና ሰጠ።


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ተቋም (Global Green Growth Institues) ጋር በመተባበር የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።


የስልጠናው ዋና ዓላማ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን አስመልክቶ የጋዜጠኞችን አቅም ለማጎልበት ነው። 


መገናኛ ብዙኃን ህብረተሰቡ በአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ከማሳወቅ እና ከማስተማር አንፃር የማይተካ ሚና የሚጫወቱ እንደመሆናቸው መጠን ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጓዴ ልማት ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ስልጠናው መገናኛ ብዙኃን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ተረድተው በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ ዘገባዎችን እንዲሰሩ ይረዳል ብለዋል።