ባለሥልጣኑ ከማስታወቂያ ዘርፍ አካላት ጋር ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ባለሥልጣኑ ከማስታወቂያ ዘርፍ አካላት ጋር ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት በማስታወቂያ ክትትል ውጤቶች ላይ እንዲሁም  ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው  ጉዳዮች ዙሪያ ከመገናኛ ብዙኃን የማስታወቂያ ክፍል አመራሮች፣ ከማስታወቂያ  ድርጅት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር  ውይይት አካሂዷል፡፡

በወይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ  የማስታወቂያ አሰራጭ ብሮድካስተሮች፣ የማስታወቂያ ወኪሎች እና የመንግስት ተቆጣጣሪ ተቋማት የማስታወቂያ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ በመዳሰስ በክትትል በተገኙ ውጤቶች ላይ እንዲሁም  ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልባቸው  ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ውይይት በማድረግ መልካም አፈፃፀሞችን ለማስቀጠል እንዲሁም የተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ደግሞ ለቀጣይ  እርምጃ ተወስዶባቸው እንዲሻሻሉ ለማስቻል  መድረኩ እንደተዘጋጀ ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የማስታወቂያው ዘርፍ የሚያከናውናቸው ስራዎች ህግን የተከተሉ፣ ለስህተት እድል የማይሰጡ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ተመራጭ  እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በኃላፊነት መስራት ነፃነትን ያጎናፅፋልና የማስታወቂያ ዘርፉ በኃላፊነት የሚንቀሳቀስ  እና ራሱን የሚመራ እንዲሁም ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ተናቦ የሚሰራ መሆን አለበት ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ  አሳስበዋል፡፡

በወይይት መድረኩ የተለያዩ ዘርፎች የተቆጣጣሪ ተቋማት ማለትም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የትምህርና ስልጠና ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ የምግብና መድሐኒት ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ባለፉት ስድስት ወራት በማስታወቂያ ክትትል፣ በኢንስፔክሽን እንዲሁም በጥቆማ እና ቅሬታ ስርዓት በተገኙ ውጤቶች ላይ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ወይይት  ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ላይም ህጋዊ ሰነዶችን ሳያረጋግጡ ማስታወቂያ ማሰራጨት፣ ማስታወቂያን ከሌሎች ፕሮግራሞች ያለመለየት፣ በህግ የተቀመጠውን የጊዜ ምጣኔን አለማክበር እንዲሁም  ዜናን በማስታወቂያ ማቋረጥ የተስተዋሉ ዋና ዋና ክፍተቶች መሆናቸው  ተጠቁሟል፡፡

በሪፖረቱ የተገለፁ ክፍተቶች ወደፊት እንዳይደገሙ  ለማድረግ  እንዲሁም ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልበቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ወይይት ተደርጓል፡፡ በወይይቱም የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት የማስታወቂያው ዘርፍ ራሱን በራሱ እንዲመራ ለማስቻል  የማስታወቂያ ምክር ቤቱን ማጠናከር  እንደሚያስፈልግ ተገልል፡፡

መጨረሻም በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶ ወይይቱ ተጠናቋል፡፡