የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን ህጎች ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጠ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን ህጎች ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአለም አቀፍ እና በሀገር  አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ህጎች እንዲሁም ተያያዥ ህጎች ዙሪያ   ለሰራተኞቹ ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠናው ዓላማ ሰራተኞቹ በነዚህ ህጎች ዙርያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው።

ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ  የመገናኛ  ብዙኃን እና ተያያዥ ህጎችን ጠንቅቆ ያላወቀ ባለሙያ ህጎቹን ተግባራዊ ለማድረግ ስለሚቸገር ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች  በህጎቹ ዙሪያ በቂ  ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

ሰራተኞች በነዚህ ህጎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ባለሥልጣኑ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ይሰጣል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ፤ሆኖም ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ በህጎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር በግል የተለያዩ ህጎችን በማንበብ ግንዛቤ ማዳበር ያስፈልጋል ብለዋል።

ሰራተኞቹም ስልጠናው በህጎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንደረዳቸው ገልፀው ከስልጠናው በተጨማሪም በራሳቸው ጥረት ሁሉንም ህጎች ለማወቅ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።