የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣የኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መ|ቤት በጋራ በመሆን በሆለታ ከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
የችግኝ ተከላው የተካሄደው የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ ጋር ተያይዞ ችግኞቹ በቀላሉ የሚፀድቁበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ሀገሪቱ የያዘችው የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ላይ አሸራን ለማስቀመጥ ነው፡፡
ዘሬ ጧት ከሶስት ሰዓት ጀምሮ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሶስቱ ተቋማት ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ ሰራተኞቹ መሰል የችግኝ ተከላ ፕሮገራሞች ኢትዮጵያ ለምትገነባቸው ታላላቅ የሃይል ፐሮጀክቶች እና ልማቶች ተፈጥሯዊ ሚዛን በመስጠትና ዘላቂነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል፡፡
የችግኝ ተከላ ፕሮገራሙ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ በሚሞላበት በዚህ ወቅት ማካሄዳቸው የሃገሪቱን የዝናብ ወይም የውሃ መጠን ለማሳደግ የሚረዳ ተግባር እንደመሆኑ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀዋል፡፡