"ሀገራዊ እሴቶችን ለማጎልበት የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው" መዋዕዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"ሀገራዊ እሴቶችን ለማጎልበት የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው" መዋዕዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ሀገራዊ እሴቶችን ለማጎልበት የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን  በጠ/ሚኒስቴር /ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር መዋዕዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከማህበረሰብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ኃላፊዎች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች እና በማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ሚና ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በጠቅላይ ሚኒስቴር /ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር መዋዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሀገራዊ እሴቶችን በማህበረሰቡ ቋንቋ ለአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የማህብበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የማህበረሰብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለሀገር አወንታዊ ፋይዳ ባላቸዉ ማለትም በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች እና ብሔራዊ ጥቅሞች እንዲሁም ሀገራዊ እሴቶች ላይ ቅድሚያ በመስጠት በአካባቢው ቋንቋ  ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን በሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማይሸፈኑ አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ በማድረስ የማህበረሰቡን ወግ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲዳብር ከመስራት በተጨማሪ የማህበረሰቡ ትስስር እንዲጠናከር እና ሰላም እንዲሰፍን ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለሥልጣኑ የውይይት መድረክ በማዘጋጀቱ አመስግነው የአቅም ውስንንት፤የቴክኒክ ብልሽት እና የስርጭት መቆራረጥ፤የሚዲያ ቁሳቁስ እና የባለሙያ እጥረት ለስራቸው እንቅፋት አንደሆነባቸው በውይይቱ አንስተዋል፡፡