“ከጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የፀዳች ሀገር ለመፍጠር  የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል” አቶ መሐመድ እድሪስ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ከጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የፀዳች ሀገር ለመፍጠር  የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋልአቶ መሐመድ እድሪስ

 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢንተርናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (IMS) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች የሚኒ ሚዲያ አባላት መምህራንና ተማሪዎች በጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ መከላከያ መንገዶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ከጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የፀዳችና የበለፀገች ሀገር ለመፍጠር  የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲታወቅና ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማስቻል መሰል መድረኮች በተለያየ ጊዜ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ "ጥላቻን የምንመክተው ራሳችን፣ አካባቢያችንንና ማህበረሰባችንን ከጥላቻ ስናርቅ ነው" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ ተማሪዎች የሚዲያና የመረጃ አጠቃቀም ክህሎታቸውን በማሳደግ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና እንደሆነ ተናግረው፤ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች ማካፈል እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ሰልጣኝ ተማሪዎች በበኩላቸው ስልጠናው የሚዲያና የመረጃ አጠቃቀም ክህሎታቸውን በማሳደግ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።

የማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩላቸው፣ አለም አንድ መንደር እየሆነች በመጣችበት በዚህ ወቅት የምናገኘውን መረጃ እውነታነት ሳናረጋግጥ ባለማጋራት ራስን፣ ማህበረሰብን ብሎም ሀገርን ከጥፋት መታደግ እንደሚያስፈልግ እና ማህበራዊ ሚዲያን በኃላፊነት መጠቀም እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ ከሁሉም /ከተሞች ከሚገኙ 25 የሁለተኛ ደረጃ /ቤቶች የተውጣጡ 100 የሚደርሱ የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎችና መምህራን የተሳተፉ ሲሆን የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።