የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም(UNDP) ኃላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ጎበኙ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መስከረም 25 2014

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የእርስበርስ ግንኙነትና ትብብር እንዲጠናከርና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪን ለማጎልበት እንዲሁም ከዚህ በፊት ላበረከቷቸው አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ባለሥልጣኑን ጎብኝተዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ያደረጉባቸውን የጥሪ ማዕከል፣ የሚዲያ ክትትል፣ የቴክኒክና ሌሎችንም የስራ ክፍሎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ባዩት ነገር መደሰታቸውንና ወደ ፊትም ትብብራቸውንና የእርስበርስ ግንኙነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

የባለሥልጣኑ የስራ ኃላፊዎችም  ባለሥልጣኑ UNDP ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና በትብብር የመስራት ልምዱን ይበልጥ በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት እነደሚሰራ ገልጸው ከዚህ በፊት ላበረክቱት አስተዋጽኦ በማመስገን  ዕወቅና ሠጥተዋል፡፡