የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ፍትህ ለሁሉም ኢትዮጵያ (Justice for All - P.F.E) በመገናኛ ብዙኃን እድገት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 05 2014 ዓ.ም

ተቋማቱ ከዚህ በፊት የሚዲያ ኢንዱስትሪውን እድገት አስመልክቶ የጋራ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በመሆኑም በጥናቱ በተለዩ ጉዳዮች፣ በሚዲያ ሕጎችና አሰራሮች እንዲሁም በሚዲያ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ወቅት ፍትህ ለሁሉም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙት የመገናኛ ብዙኃንን የሚገዙ ሕጎች፣ አሰራሮች እና ተግዳሮቶችን የሚዳስስ "የኢፌዴሪ የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲና ሕጎች፤ ተግዳሮቶች ክፍተቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች" የሚል ርዕስ የተሰጠው የጥናት ሰነድ አስረክቧል።

በመጨረሻም ከዚህ በፊት የነበራቸውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በሚዲያው እድገትና መስፋፋት ዙሪያ ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።