የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ተቀብለው ማስተላለፍ ወይም ሊንክ ማድረግ ከዛሬ ጀምሮ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ፡፡

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 19 2014 ዓ.ም

የሬዲዮ ሞገድ በሀገራችን በጣም ውስን መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሬድዮ ባለፈቃዶች በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ይዘቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ ማድረግ አለባቸው። በዚህ መርህ መሰረት የሬድዮ ሞገዶቹ ለባለፈቃዶቹ ለውድድር ባቀረቡት ሰነድ በግልፅ ጨረታ የተሰጡ ናቸው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጭ ሚዲያ ፕሮግራሞችን በቀጥታ (ሊንክ) በማድረግ የሚያስተላልፉ ኤፍ ኤሞች ተመልክተናል ሲሉ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ አስታውቀዋል። ባለፈቃዶቹ ውስን የህዝብ ሀብት የሆነው የሬድዮ ሞገድ ከታሰበለት አላማ ውጪ ከውጭ ሚዲያዎች በሊንክ የሚያስተላልፏቸውን ፕሮግራሞች ከዛሬ ቀን ጀምሮ በጣቢያቸው ማስተላለፍ እንዲያቆሙ መወሰኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ሚዲያ ፕሮግራሞችን በቀጥታ ተቀብለው ሲያስተላልፉ፤ ጣቢያዎቹ ቁጥጥራቸው የላላና የመጣላቸውን እንዳለ ከማስተላለፋቸውም ባለፈ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበና ብሔራዊ ጥቅምን የሚጎዳ ነው። በተጨማሪም ሊንክ ተደርገው የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ላይ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለሬድዮ ጣቢያዎቹ ተገቢውን ግብረ መልስ ለመስጠትና በህግ የተጣለበትን ቁጥጥር የማድረግ ኃላፊነት ለመወጣት ባለመቻሉ ክልከላው እንደተላለፈ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጨምረው ገልፀዋል፡፡