የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከUN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሥርዓተ ጾታ ምላሽ ሰጭ መመሪያ ዙሪያ እና የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ለማጎልበት የሶስት ቀን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 27 2014 ዓ.ም.

የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሴት እና ወንድ ባለሙያዎች ስለሚያገኟቸው እና ስለሚያሰጧቸው ዕድሎች፤ መገናኛ ብዙኃን በይዘታቸው ወንዶች እና ሴቶችን የሚዘግቡበትና የሚቀርጹበት ዕይታ፤ የጋዜጠኞች ዘገባዎች የሁለቱም ጾታዎች ድምጽ እና ሃሳብ በእኩል መጠን ማስተናገድ ዙሪያ ላይ አቅም መገንባት ያተኮረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ የጾታ እኩልነት፣ የወንዶች እና ሴቶችን ድምጽ እና ሃሳብ በእኩል መጠን ለማስተናገድ እየተሰራ እንደሚገኝ፤ ነገር ግን አሁንም በተሻለ መልኩ መስራት እንደሚቻልና ይኸንን ለማስፈጸምም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተሳታፊዎች ከስልጠናው የሚያገኙትን ፍሬ በሚረዱበት፣ በሚገልጹበት እና ለማህበረሰቡ በሚያሳዉቁበት መንገድ ከስልጠናው ልምድ እንደሚያካብቱ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡

በስልጠና መርሐ-ግብሩ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የመገናኛ ብዙኃን የፕሮግራም ኃላፊዎች እና ጋዜጠኞች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡