የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከህዝብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች  ጋር  ሚዲያዎች በሚያሰራጯቸው ፕሮግራሞች ላይ በሚያደርገው የክትትል ስራ ውጤት  ዙርያ ውይይት አካሄደ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

የኢ... የህዝብ እና የማህበረሰብ መገናኛ ክትትል ዳይሬክቶሬት የሚያከናውናቸውን የክትትል አግባቦችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ከህዝብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ከፍተኛ አዘጋጆች ጋር ተወያየ

የውይይቱ ዋና ዓላማ  ሀገራችን እያካሄደች ያለውን የህልውና ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ባለሥልጣኑ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘውን የክትትል ስራ ለመገናኛ ብዙኃኑ ለማስረፅና የጋራ መግባባት ላይ  ለመድረስ እንዲረዳ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

.መብ.. /ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህልውና ዘመቻውን ተከትሎ የሚሰሩ ዘገባዎች ላይ የተወሰኑ ለውጦች ቢኖሩም በቂ ባለመሆናቸዉ አሁን የምንመለከታቸውን ተስፋ ሰጪ ነገሮች ለማሻሻል የክትትል ስራውን አጠናክረን በማስቀጠል ሀገርን በማዳን ዘመቻው ላይ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል። 

መገናኛ ብዙኃኑም ዜናዎችን ከመስራት በተጨማሪ ሌሎች የመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ የህልውና ዘመቻውን የሚያሳዩ ዘገባዎች መስራት እንዲሁም ከህልውና ዘመቻው ጋር ተያይዞ በሀገራችን ላይ የሚመጡትን ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች መመከት መቻል እንዳለባቸው አቶ ዮናታን ጨምረው ተናግረዋል።

ተሳታፊዎችም ሀገራችን ያለችበትን የህልውና ዘመቻ ለመደገፍ ከባለሥልጣኑ ጋር  ተባብሮ መስራት ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ከውይይቱ  ሰፊ ግንዛቤ  ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።