የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 20 ቀን 2014 .

ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ ማስታዎቂያዎችን በተመለከተ በቅንጅት ለመስራት ነው።

በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ የሚሰራጩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስታዎቂያዎችን ለህብረተሰቡ ተገቢውንና ትክክለኛ መረጃ ለማድረስ እንዲያስችል፤ የሚያስፈጽሟቸው እና ቁጥጥር የሚያደርጉባቸውን ህጎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እና ማህበረሰቡን ካልተገባ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንግልት ለመጠበቅ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ከዚህ በፊት ያለን በህግ የተሰጠን ስልጣን እና ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ በሁለቱም ተቋማት መካከል ተቀናጀተን በምንሰራባቸው ጊዜ የግንኙነት አግባቦችን ለመወሰን፣ የመረጃ ልውውጣችን አግባቡን በጠበቀ መሰረት እንድናደርግ እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን የሚገኙ ቅሬታዎችን ለመፍታት ተቀናጅተን መስራት በምንችልበት ሁኔታ ስርአት ለመፍጠር ነው ይህንን የመግባቢያ ሰነድ የምንፈራረመው ብለዋል።