አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ-ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ የቆዩ አስር አንጋፋ ባለሙያዎች እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የእድገት የሃሳብ ፎኖተ-ካርታ ላይ ምክክር እደርገዋል፡፡

የሚዲያው እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ ያተኮረው ውይይት መድረክ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተዘጋጀ ሲሆን አራተኛውየመንገስት አካል እስከመባልየደረሰው ተፅኖ ፈጣሪ ዘርፍ የሚመራበትን አቅጣጫ በአንጋፋዎቹ እይታ ውስጥ ለመመልከት ነው፡፡

አንጋፋ ሙሁራኑ መገናኛ ብዙኃን በአሁን ሰዓት በብዙ እድሎች የታጀበ ሆኖ ሳለ የህብረተሰቡን ስነ ልቦና እና በሃገሪቱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በተቀናጀ መልኩ መስራት ላይ ትልቅ ክፍተት እንደሚታይ ያነሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ባግባቡ መከበር ከተጀመረ ወዲህ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተሻለ እና የሚያበረታታ ሥራ ለማከናወን ትጋት ማሳየታቸው የማይካድ ቢሆንም በሰላም ግንባታ፣ ተግባቦት፣ ዲሞክራሲን ከማዳበር አኳያ ዛሬም ብዙ እንደሚቀራቸ \ርንጉሴ ተፈራ በበኩላቸው ያነሳሉ፡፡

50 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በዲፕሎማሲ ሰራ ለይ ያገለገሉት አቶ ማዕረጉ በዛብህ ከምዕራቡ ዓለም የተኮረጀ እና የሀገሪቱን ህዝቦች ባህል፣ ትውፊት እና ስነ ልቦና ያላከበረ አሰራር ውስጥ መዘፈቅ እንደ ቀላል መታለፍ ያለበት ጉዳይ እይደለም ይላሉ፡፡ "የሌሎች ባህል ናፋቂነት በሚዲያዎች ይታያል"ሲሉም ይገልፃሉ፡፡

የሸገር ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ መዓዛ ብሩ የበኩላቸውን ሲናገሩ አሁን ላይ ያሉ ብዙ የፖለቲካ አንቂዎች ሚዲያው እንዲሆን የሚፈልጉት እና የሚዘውሩበት ሪዮት አለማዊ ሃሳብ ከገለልተኝነት መርህ አንፃር ምን ያክል ያራምድናል የሚለውን ጥያቄ ማጤን ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

19 ዓመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሆና ያገለገሉት እና አሁን ላይ በኮሚኒቲ ዲቨለፕመንት ስራ ላይ የተሰማሩት | አባይነሽ ብሩ የመገናኛ ብዙኃን የቋንቋ አጠቃቀም የማህበረሰብን ክብር ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ ለማሻሻል ጥረት አለመደረጉ የሚያሳዝን ነው ሲሉ ይገልፃሉ፡፡