ባለሥልጣኑ ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች፣ በሙያ ስነ-ምግባር መርሆች እና በማህበረሰብ ብሮድካስት ሚና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከጀስቲስ ፎር ኦል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች፣ በሙያ ስነ-ምግባር መርሆች እና በማህበረሰብ ብሮድካስት ሚና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የእርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የሚረዳ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ተቋም (Global Green Growth Institues) ጋር በመተባበር የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ አዘጋገብን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአልጀዚራ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ በአረብኛ ቋንቋ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ባለሥልጣኑ ከ UN WOMEN ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ስርዓተ ፆታን ያገናዘበ የመገናኛ ብዙኃን የግጭት አዘጋገብ መመሪያ አዘጋጅቶ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡:
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለፉት 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት ሁለቱ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ ማስታዎቂያዎችን በተመለከተ በቅንጅት ለመስራት ነው።
ኢ.መ.ብ.ባ ከ UN Women ጋር በመተባበር በስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ማስታወቂያ ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
የኢ.መ.ብ.ባ የህዝብ እና የማህበረሰብ መገናኛ ክትትል ዳይሬክቶሬት የሚያከናውናቸውን የክትትል አግባቦችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ከህዝብ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ከፍተኛ አዘጋጆች ጋር ተወያየ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች “ደማችንን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ዙር ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሐግብር አካሄዱ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዲያውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ኤክስፖዎች በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳሉ፤ በሀገራችን ደረጃም አሁን መጀመሩ ለሚዲያው እድገት ትልቅ እምርታ ነው። ስለሆነም ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።
በውይይቱ የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በእቅድ የተያዙ ስራዎች አፈጻጸማቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች እና የተስተዋሉ ክፍተቶች በሪፖርቱ ተነስተዋል። ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ደግሞ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት እንዴት ማሻሻል እንደሚገባ እና ወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የስልጠናው ዋና አላማ ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ ምላሽ ሰጭ መመሪያ አተገባበር፤ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሴት እና ወንድ ባለሙያዎች ስለሚያገኟቸው እና ስለሚያሰጧቸው ዕድሎች፤ መገናኛ ብዙኃን በይዘታቸው ወንዶች እና ሴቶችን የሚዘግቡበትና የሚቀርጹበት ዕይታ፤ የጋዜጠኞች ዘገባዎች የሁለቱም ጾታዎች ድምጽ እና ሃሳብ በእኩል መጠን ማስተናገድ ዙሪያ ላይ አቅም መገንባት ያተኮረ ነው፡፡
የሬዲዮ ሞገድ በሀገራችን በጣም ውስን መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሬድዮ ባለፈቃዶች በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ይዘቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ ማድረግ አለባቸው።
ተቋማቱ ከዚህ በፊት የሚዲያ ኢንዱስትሪውን እድገት አስመልክቶ የጋራ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በመሆኑም በጥናቱ በተለዩ ጉዳዮች፣ በሚዲያ ሕጎችና አሰራሮች እንዲሁም በሚዲያ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
አይ. ኤም. ኤስ. (IMS) ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋር የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በትብብር የሚሰራ አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ተቋሙ ከባለሥልጣኑ ስር ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ክትትል(የሞኒተሪንግ) ክፍሎች ጋር በመሆን የክትትል ስራን ለማሳደግ፣ ለማዘመን እና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪውን ለማብቃት ከባለሥልጣኑ ጋር እየሰሩ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የእርስበርስ ግንኙነትና ትብብር እንዲጠናከርና የመገናኛ ብዙኃን ኢንዱስትሪን ለማጎልበት እንዲሁም ከዚህ በፊት ላበረከቷቸው አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ባለሥልጣኑን ጎብኝተዋል፡፡
“ሃገርን ለማዳን ተልዕኮ ወስዶ መስራት ለህዝብ ያለን ወገንተኝነት ማሳየት ነው፡፡ይህ ግዜ ወገንተኝነታችንን የምናሳይበት ሰዓት ነው፡፡ ስሙ የግል ይሁን እንጂ ሚዲያ የህዝብ ሃብት መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው” አቶ መሃመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ የቆዩ አስር አንጋፋ ባለሙያዎች እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የእድገት የሃሳብ ፎኖተ-ካርታ ላይ ምክክር እደርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣የኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መ|ቤት በጋራ በመሆን በሆለታ ከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት በዱር በገደሉ ደሙን እያፈሰሰና አጥንቱን እየከሰከሰ ኢትዮጵያና ልጆቿን እየጠበቀ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከሙያዊ ድጋፋቸው በተጨማሪ የአንድ ወር ደሞዛቸውን በመለገስ ከጎኑ መሆናችውን አሳይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት የሚከፍለው ዋጋ ታሳቢ አድረገው በማንኛውም ግዜና ሁኔታ ከጎኑ መሆናቸውን ለመግለፅ ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም የደም ልገሳ አካጊሂደዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከታተል የሚያስችለውን የቅሬታና እና ጥቆማ መቀበያ የጥሪ ማዕከል ገንብቶ ስራ ጀምሯል
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2013 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2014 ዓ.ም የእቅድ አቅጣጫ ዙሪያ ሰረተኞቹን እያወያየ ይገናኛል
አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ ምክክር አደረጉ
መገናኛ ብዙሃን የምርጫውን ሂደት ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረና ከፍ ባለ አገራዊ ስሜት መዘገባቸው የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በዚህ የጥሞና ወቅት በመገናኛ ብዙኃን እንዳይተላለፍ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማሳሰቡን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታዉቋል።
ዓለም ፐሬስ ነፃነት ቀን ለ30ኛ ግዜ "መረጃ ለህዝብ ጥቅም" በሊል ርዕስ ሲከበር ይውላል፡፡ ባለድርሻ አካላት ላይት ሆቴል በተዘጋጀው ኮንፍረንስ ተሰባስበዋል፡፡
ለውይይት የቀረቡት አራቱ መመሪያዎች የንግድ፣ የህዝብ፣የበይነ-መረብ የማህበረሰብ እና ልዩ የህዝብ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት መመሪያዎች ናቸው፡፡